ኢዮብ 11:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታርፋለህ፥ የሚዋጋህም የለም፤ ብዙ ሰዎችም ይመጣሉ፤ ልመናም ያቀርቡልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለ አንዳች ሥጋት ትተኛለህ፤ ብዙ ሰዎችም ደጅ ይጠኑሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፥ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንንም ሳትፈራ ትተኛለህ፤ ብዙ ሰዎችም በአንተ ፊት ሞገስ ማግኘትን ይፈልጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፥ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል። |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ግብፅና የኢትዮጵያ ንግዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይገዙልሃል፤ እጆቻቸውን ታስረው በኋላህ ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፤ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች እየተንቀጠቀጡ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብለሽም ትጠሪያለሽ።
እንግዲህ ለአሕዛብ ንጥቂያ አይሆኑም፤ የምድርም አራዊት አይበሉአቸዋም፤ ተዘልለውም ይቀመጣሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።
በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ትተኛላችሁ፤ የሚያስፈራችሁም የለም፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድራችሁ አጠፋለሁ።
የእስራኤል ቅሬታ ኃጢአትን አይሠሩም፥ ሐሰትንም አይናገሩም፥ በአፋቸውም ውስጥ ተንኰለኛ ምላስ አይገኝም፣ እነርሱም ይሰማራሉ፥ ይመሰጉማል፥ የሚያስፈራቸውም የለም።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።