La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 37:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ተመ​ል​ሰው ይህ​ችን ከተማ ይዋ​ጉ​አ​ታል፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባቢሎናውያንም ተመልሰው ይህችን ከተማ ይወጓታል፤ ይዘውም ያቃጥሏታል።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከለዳውያንም ተመልሰው ይህችን ከተማ ይዋጉአታል ይይዟታልም በእሳትም ያቃጥሉአታል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያ በኋላ ባቢሎናውያን ተመልሰው ይመጣሉ፤ አደጋም ጥለው ከተማይቱን ይይዛሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከለዳውያንም ተመልሰው ይህችን ከተማ ይዋጉአታል ይይዙአትማል በእሳትም ያቃጥሉአታል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 37:8
9 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ይችን ከተማ የሚ​ወጉ ከለ​ዳ​ው​ያን ይመ​ጣሉ፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም በእ​ሳት ያነ​ድ​ዱ​አ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለበ​ዓል ያጠ​ኑ​ባ​ቸ​ውን፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸ​ውን ቤቶች ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ተላ​ልፋ ትሰ​ጣ​ለች፤ ይይ​ዛ​ታል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላ​ታል።


ነገር ግን እና​ን​ተን የሚ​ወ​ጉ​ትን የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ጭፍራ ሁሉ ብት​መቱ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጥቂት ተወ​ግ​ተው ያል​ሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በስ​ፍ​ራው ይነ​ሣሉ፤ ይህ​ቺ​ንም ሀገር በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።”


ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ባት​ወጣ ግን፥ ይች ከተማ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ትሰ​ጣ​ለች፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ አን​ተም ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም” አለው።


ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንና ልጆ​ች​ህ​ንም ሁሉ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ያወ​ጣሉ፤ አን​ተም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትያ​ዛ​ለህ እንጂ ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት ትቃ​ጠ​ላ​ለች።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ በር​ግጥ ትሰ​ጣ​ለች፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል።”