ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
ኤርምያስ 21:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለይሁዳ ንጉሥ ቤትም እንዲህ በል፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ዘሮች ለሆኑት ለይሁዳ ንጉሣዊ ቤተሰብ እንድነግራቸው እግዚአብሔር የሰጠኝ ቃል ይህ ነው፦ “እኔ እግዚአብሔር የምነግራችሁን አድምጡ፤ በየማለዳው ፍትሕ እንዳይጓደል አድርጉ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራበት ጠብቁ፤ ይህን ባታደርጉ ግን ከምትሠሩት ክፋት የተነሣ ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ሊያጠፋውም የሚችል አይኖርም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
እንዲህም በላቸው፥ “በእነዚህ በሮች የምትገቡ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፥ ይሁዳም ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።”
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፥ “ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚያለቅስለት ለሌለው ለዚያ ሰው ወዮለት!