La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 65:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኒህ ሕዝብ ዘወ​ትር የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡኝ ናቸው፤ እነ​ርሱ በአ​ት​ክ​ልት ውስጥ የሚ​ሠዉ በጡ​ብም ላይ ለአ​ጋ​ን​ንት የሚ​ያ​ጥኑ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣ በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህ ሕዝብ ዘወትር በፊቴ ቁጣን ይቀሰቅሳሉ፥ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ፥ በጡብም ላይ የሚያጥኑ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነዚህም ሰዎች በአትክልት ቦታ ውስጥ መሥዋዕት በመሠዋትና በጡብ ላይ በፊቴ ሁልጊዜ ዕጣን በማጠን እኔን የሚያስቈጡኝ ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፥ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የምያጥኑ፥

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 65:3
20 Referencias Cruzadas  

በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


ነገር ግን እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ ያለ​ውን ሁሉ ዳስስ፤ በእ​ው​ነት በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ብ​ሃል።”


ነገር ግን አሁን እጅ​ህን ዘር​ግ​ተህ አጥ​ን​ቱ​ንና ሥጋ​ውን ዳስስ፤ በእ​ው​ነት በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ብ​ሃል” ብሎ መለሰ።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ያፍ​ራ​ሉና፥ በፈ​ለ​ጉ​አ​ቸ​ውም የአ​ድ​ባር ዛፎች ዕፍ​ረት ይይ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ ይሁ​ዳም ወድ​ቃ​ለ​ችና፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ዐመ​ፅን ስለ​ሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ዘ​ዙም።


“በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ውስጥ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ጠ​ሩና የሚ​ያ​ነጹ፥ በም​ግብ ቦታም የእ​ሪ​ያን ሥጋ፥ አስ​ጸ​ያፊ ነገ​ር​ንም አይ​ጥ​ንም የሚ​በሉ በአ​ን​ድ​ነት ይጠ​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በን​ጉሡ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን እን​ዲህ አለኝ፥ “ከዳ​ተ​ኛ​ዪቱ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ች​ውን አየ​ህን? ወደ ረዘ​መው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመ​ለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚ​ያም አመ​ነ​ዘ​ረች።


እሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጄን ወደ አነ​ሣ​ሁ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ከፍ ያለ​ውን ኮረ​ብታ ሁሉ፥ ቅጠ​ላ​ማ​ው​ንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚ​ያም ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ሠዉ፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ኝን፤ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ በዚ​ያም ደግሞ ጣፋ​ጩን ሽታ​ቸ​ውን አደ​ረጉ፤ በዚ​ያም የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አፈ​ሰሱ።


ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሜዳ የሚ​ያ​ር​ዱ​ትን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ያመ​ጡ​ታል፤ ወደ ካህ​ኑም አም​ጥ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለድ​ኅ​ነት መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዉ​ታል።


አም​ላክ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ኑኝ፤ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝ​ብም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።