La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 39:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ፣ የባልዳን ልጅ፣ መሮዳክ ባልዳን የሕዝቅያስን መታመምና መፈወስ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ዘመን የባቢሎን ንጉሥ የባላዳን ልጅ መሮዳክ ባላዳን ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ መዳኑን ሰማ፤ ስለዚህም ከገጸ በረከት ጋር ደብዳቤ ላከለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 39:1
11 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም፥ “አባቱ ቸር​ነ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ልኝ እኔ ለና​ዖስ ልጅ ለሐ​ኖን ቸር​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም ስለ አባቱ ያጽ​ና​ኑት ዘንድ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን ላከ፤ የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች ወደ አሞን ልጆች ሀገር መጡ።


ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤


ብዙ​ዎ​ቹም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ይዘው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመጡ ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እር​ሱም ከዚህ ነገር በኋላ በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።


ሕዝ​ቅ​ያስ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ቸር​ነት መጠን አላ​ደ​ረ​ገም፤ ልቡም ኮራ፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ር​ሱና በይ​ሁዳ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ቍጣ ሆነ።


ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን መሳ​ፍ​ንት መል​እ​ክ​ተ​ኞች በሀ​ገሩ ላይ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተ​ላኩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ነ​ውና በልቡ ያለ​ውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።


የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።


የመ​ን​ግ​ሥ​ታት ክብር፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም የት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ትም​ክ​ሕት የሆ​ነች ባቢ​ሎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ትሆ​ና​ለች።


ይህ​ንም ሙሾ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ታነ​ሣ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፥ “አስ​ጨ​ናቂ እን​ዴት ዐረፈ! አስ​ገ​ባ​ሪም እን​ዴት ጸጥ አለ!


እነሆ፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሀገር አሦ​ራ​ው​ያን አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ታ​ልና፤ ግን​ብ​ዋም ወድ​ቆ​አል፤