ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና።
ኢሳይያስ 32:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየዓመቱ የኀዘን በዓል መታሰቢያ አድርጉ፤ ወይን መቍረጥ አልፎአል፤ ፍሬ ማከማችትም አልቆአል፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይመጣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓመቱ ገና እንዳለፈ፣ ተደላድላችሁ የነበራችሁ ትንቀጠቀጣላችሁ፤ የወይን ተክል ፍሬ አይሰጥም፤ የፍራፍሬም ወቅት አይመጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቁረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በኑሮአችሁ የተማመናችሁ ሴቶች ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተስፋ የሚያስቈርጥ ጭንቀት ይደርስባችኋል፤ ከወይንም ሆነ ከሌላው ተክል ሁሉ በቂ ፍሬ አታገኙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፥ ወይንን መቍረጥ ይጠፋልና፥ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ። |
ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና።
በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል።
አዝመራቸውን ይሰበስባሉ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠልም ይረግፋል፤ ሰጠኋቸው፤ አለፈባቸውም።
እርስዋም፥ “ወዳጆች የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ሁሉ ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ምስክርም ይሆኑ ዘንድ አኖራቸዋለሁ፤ የምድረ በዳም አራዊትና የሰማይ ወፎች፥ የምድር ተንቀሳቃሾችም ይበሉታል።
የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤ ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤
ወይኑ ደርቆአል፤ በለሱም ጠፍቶአል፤ ሮማኑና ተምሩ፥ እንኮዩም፥ የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል።
እናንተ ሰካራሞች፥ ንቁ፤ ለመስከርም ወይንን የምትጠጡ እናንተ ሁላችሁ! ተድላና ደስታ ከአፋችሁ ጠፍትዋልና አልቅሱ፤ እዘኑም።
ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥
ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።