አንተስ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ፤ እንዲህም አልህ፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ጥግ እወጣለሁ፤ ረጃጅሞችንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ሀገሩም ዳርቻና ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።
ኢሳይያስ 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜ ተራሮችና ኮረብቶች፥ ዛፎችም ይጠፋሉ። ነፍስና ሥጋንም ይበላል፤ የሚሸሽም ከሚነድድ የእሳት ነበልባል እንደሚሸሽ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፣ የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፣ ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕመምተኛ እየመነመነ እንደሚሞት፤ የደኑን ክብርና የለማውን ዕርሻ፤ ነፍስና ሥጋንም ፈጽሞ ያጠፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርቱ ደዌ ሰውን አሰልስሎ እንደሚገድል፥ የተዋቡ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖቹና ለምለም የእርሻ ቦታዎቹ ይደመሰሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከነፍስም እስከ ሥጋ ድረስ የዱሩንና የሚያፈራውን እርሻ ክብር ይበላል፥ ይህም የታመመ ሰው እንደሚሰለስል ይሆናል። |
አንተስ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ፤ እንዲህም አልህ፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ጥግ እወጣለሁ፤ ረጃጅሞችንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ሀገሩም ዳርቻና ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።
ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበት መንገድም እመልስሃለሁ።
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤
ኀጢአት እንደ እሳት ይነድዳል፤ እሳት እንደ በላችው ደረቅ ሣር ይቃጠላል፤ እንደ ዱር ሣርም ይቃጠላል፤ በተራራዎች ዙሪያ ያለው ሁሉ አብሮ ይቃጠላል።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።