ሆሴዕ 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፤ ለራሱም ዕንቅፋትን አኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬም ከጣዖት ጋራ ተጣምሯል፤ እስኪ ተዉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጣምሯል፤ እርሱንስ ተወው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ከጣዖት አምልኮ ጋር ስለ ተጣመሩ ተዉአቸው የፈለጉትን ያድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤፍሬም ከጣዖታት ጋር ተጋጠመ፥ ተወው። |
ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤል ቤትና ይሁዳም በተንኰል ከበቡኝ፤ አሁንም እግዚአብሔር ዐወቃቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።
ዳግመኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚሠራው አምሳል ከወርቃቸውና ከብራቸው ጣዖትን ሠሩ፤ እንዲህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አልቋል።”