La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሆሴዕ 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከይ​ሁዳ ጋር ይዋ​ቀ​ሳል፤ ያዕ​ቆ​ብ​ንም እንደ መን​ገዱ ይበ​ቀ​ለ​ዋል፤ እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፍ​ለ​ዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በማሕፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፤ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋራ ታገለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፤ እንደ ሥራውም ይመልስለታል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያዕቆብ ገና በማሕፀን ሳለ የመንትያ ወንድሙን ለመቅደም ተረከዙን ያዘ፤ ካደገም በኋላ አምላክን ይዞ “አለቅም” አለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ክርክር አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፥ እንደ ሥራውም ይመልስለታል።

Ver Capítulo



ሆሴዕ 12:3
14 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድሙ ወጣ፤ በእ​ጁም የዔ​ሳ​ውን ተረ​ከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙ​ንም ያዕ​ቆብ ብላ ጠራ​ችው። ርብቃ ዔሳ​ው​ንና ያዕ​ቆ​ብን በወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ጊዜ ይስ​ሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ከፊ​ቱም ጣላ​ቸው፤ ከይ​ሁ​ዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸ​ውም፤ ከፊ​ቱም እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ በበ​ዝ​ባ​ዦች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።


“ስለ​ዚህ እንደ ገና ከእ​ና​ንተ ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ፤ ከል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ልጆች ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ።


አሁ​ንም ፍጻሜ በአ​ንቺ ላይ ደር​ሶ​አል። ቍጣ​ዬ​ንም እሰ​ድ​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።


አሁን በቅ​ርብ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ስ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬ​ንም እፈ​ጽ​ም​ብ​ሻ​ለሁ፤ እን​ደ​መ​ን​ገ​ድ​ሽም መጠን እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽ​ንም ሁሉ አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እንደ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ካህኑ ይሆ​ናል፤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሥራ​ቸ​ውም እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ከ​ተ​ሉት ከንቱ ነገር አስ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይ​ሁዳ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።


ሳይ​ወ​ለዱ፥ ክፉና መል​ካም ሥራም ሳይ​ሠሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መም​ረጡ በምን እንደ ሆነ ይታ​ወቅ ዘንድ፥