“የአሴር እንጀራ ወፍራም ነው፤ እርሱም ለአለቆች ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል።
“አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።
የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው፥ ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይሰጣል።
“አሴር ከምድሩ ብዙ ሀብት አግኝቶ ይበለጽጋል፤ በነገሥታት ፊት መቅረብ የሚችል ጥሩ ምግብ ያዘጋጃል።
የአሴር እንጀራው ወፍራም ነው ለነገሥታቱም ደስ የሚያሰኝ መብልን ይስጣል።
ልያም፥ “እኔ ብፅዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።
የአሴርም ልጆች፤ ኢያምን፥ ኢያሱ፥ኢዩል፥ በሪዓ፥ እኅታቸው ሳራ፤ የበሪዓ ልጆችም፤ ኮቦር፥ መልኪኤል።