La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 46:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልያ በመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ በሶ​ርያ ለያ​ዕ​ቆብ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ልጆ​ችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነ​ዚህ ናቸው፤ ወን​ዶ​ችም ሴቶ​ችም ልጆ​ችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቷም ልጅ ዲና በመስጴጦምያ ሳሉ ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ናቸው። ያዕቆብ ከልያ ያፈራቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ሠላሳ ሦስት ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልያ በመስዼጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ዲና እነዚን ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 46:15
14 Referencias Cruzadas  

ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።


ለላ​ባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ልያ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ራሔል ነበረ።


የልያ ልጆች፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤


የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች፤ ሳሬድ፥ አሎን፥ አሌል።


የጋ​ድም ልጆች፤ ስፎን፥ ሐጊ፥ ሱኒ፥ አዜን፥ አድ፥ አሮ​ሐድ፥ አር​ሔል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤