ዘፍጥረት 34:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “እኅታችንን እንደ አመንዝራ አድርገው ለምን አዋረዷት?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን፣ “ታዲያ፣ እኅታችንን እንደ ዝሙት ዐዳሪ ይድፈራት?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኅታችን ሊደረግ ይገባልን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ግን “እኅታችን እንደ አመንዝራ ሴት ትደፈርን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኅታችን ያደርግባትን? አሉ። |
ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፥ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚያም ኑር፤ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጥሁልህ ለእኔ መሥውያን ሥራ።”
ቍጣቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበርና፤ ኵርፍታቸውም ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፤ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።