La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 31:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው ዐደሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፥ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጠራ፥ እነርሱም ምግብ ተመገቡ፥ በዚያም በተራራ ሌሊቱን ሙሉ አሳለፉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በተራራውም ላይ ያዕቆብ መሥዋዕት አቀረበ፤ ሰዎቹን ሁሉ ጠርቶም ምግብ እንዲመገቡ አደረገ፤ ከበሉም በኋላ ሌሊቱን በዚያ አሳለፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያዕቆብም በተራራው ላይ መሥዋዕትን ሠዋ ወንድሞቹንም እንጀራ እንዲበሉ ጠራ እነርሱም እንጀራን በሉ በዚያም በተራራ አደሩ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 31:54
7 Referencias Cruzadas  

ሕፃ​ኑም አደገ፤ ጡት​ንም አስ​ጣ​ሉት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ጡት ባስ​ጣ​ለ​በት ቀን ትልቅ ግብ​ዣን አደ​ረገ።


ይስ​ሐ​ቅም ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በሉም፤ ጠጡም።


እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።


የሙሴ አማት ዮቶ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወሰደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እን​ጀራ ሊበሉ አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ።


አለ​ቃው ግን እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ታል፤ በበሩ ይገ​ባል፤ በዚ​ያም መን​ገድ ይወ​ጣል።”


ቈነ​ጃ​ጅ​ቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊ​ታ​ችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረ​ብታ ላይ መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ አለ​ባ​ቸ​ውና።