ልያም፥ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወደድኛል ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ዘፍጥረት 30:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፤ ስምዋንም ዲና አለቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፥ ስምዋንም ዲና አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና ብላ ጠራቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፤ ስምዋንም ዲና አለቻት። |
ልያም፥ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፤ እንግዲህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወደድኛል ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው።
ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።