ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት፤ ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው፥ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ” አለው።
ዘፍጥረት 29:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ላባን፥ “እንግዲህ ወደ እርስዋ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈጽሞአልና አለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ያዕቆብ ላባን፣ “እነሆ፤ የተባባልነው ጊዜ አብቅቷል፤ ስለዚህ ሚስቴን አስረክበኝና የባልና የሚስት ወጋችንን እናድርስ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ላባን፦ “ወደ እርሷ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈጽሞአልና” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ላባን “እነሆ፥ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈጽሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ላባን፦ ወደ እርስዋ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ ቀኔ ተፈጽሞአልና አለው። |
ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት፤ ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው፥ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ” አለው።
ለአንተ ቤት የተገዛሁልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ሰባት ዓመት ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፤ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።
ወደ እርስዋም አዘነበለ፥ “እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፥ “ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው።
ከጊዜም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዳይገባ ከለከለው።