ዘፍጥረት 23:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻም በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዕርሻውና ውስጡ የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያውያን ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በሒታውያን ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሒታውያን የነበረው እርሻ በውስጡ ካለው ዋሻ ጋር የአብርሃም የመቃብር ርስት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና። |
ከዚህም በኋላ አብርሃም ኬብሮን በምትባል በመምሬ ፊት በከነዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሣራን ቀበረ።
“እኔ በእናንተ ዘንድ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ፤ በእናንተ ዘንድ እንድገዛ የመቃብር ርስት ስጡኝ፤ ሬሳዬንም እንደ እናንተ ልቅበር።”
ልጆቹ ይስሐቅና ይስማኤልም በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እኔ ወደ ወገኖች እሰበሰባለሁ፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶች ጋር ቅበሩኝ፤ እርስዋም በከነዓን ምድር በመምሬ ፊት ያለች፥
ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር መለሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት፤ እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች፥ አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጢያዊው ከኤፍሮን ከእርሻው ጋር የገዛት ዋሻ ናት።
አባቴ ሳይሞት አምሎኛል፤ እንዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር በዚያ ቅበረኝ።’ አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።”
ንጉሡም ኦርናን፥ “እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአንተ እገዛለሁ፤ ለአምላኬም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ያለ ዋጋ አላቀርብም” አለው። ዳዊትም አውድማውንና በሬዎቹን በአምሳ ሰቅል ብር ገዛ።