ዘፍጥረት 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገና ሳይተኙም የዚያች ከተማ ሰዎች፥ ታናሹም፥ ታላቁም ቤቱን በአንድነት ከበቡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመተኛታቸውም በፊት፣ የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወንድ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ፥ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዶቹ ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ሰዎች ቤቱን ከበቡት፤ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ሳይቀሩ የከተማይቱ ወንዶች ሁሉ እዚያ ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ ቤቱን ከበቡት። |
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።