La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም አለው፥ “የሰ​ዶ​ምና የገ​ሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እጅግ ከበ​ደች፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ጩኸት እጅግ በዝቷል፤ ኀጢአታቸውም እጅግ ከፍቷል፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርም አለ፦ “የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “የሰዶምና የገሞራ ሕዝብ የሚፈጽሙት በደል ምን ያኽል እንደ ሆነ ሰምቼአለሁ፤ ኃጢአታቸውም እጅግ ከባድ መሆን አለበት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም አለ የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 18:20
14 Referencias Cruzadas  

የሰ​ዶም ሰዎች ግን ክፉ​ዎ​ችና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነበሩ።


እኛ ይህ​ችን ስፍራ እና​ጠ​ፋ​ታ​ለ​ንና፥ ጩኸ​ታ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትልቅ ሆኖ​አ​ልና፤ እና​ጠ​ፋ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልኮ​ናል።”


ገና ሳይ​ተ​ኙም የዚ​ያች ከተማ ሰዎች፥ ታና​ሹም፥ ታላ​ቁም ቤቱን በአ​ን​ድ​ነት ከበ​ቡት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደ​ረ​ግህ? የወ​ን​ድ​ምህ የአ​ቤል የደሙ ድምፅ ከም​ድር ወደ እኔ ይጮ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን እንደ ተበ​ላ​ሸች፥ ሥጋን የለ​በሱ ሁሉም በም​ድር ላይ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን እንደ አበ​ላሹ አየ።


ዛሬም ክብ​ራ​ቸው ተዋ​ር​ዷ​ልና፥ ፊታ​ቸ​ውም አፍ​ሯ​ልና ኀጢ​አ​ታ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና እንደ ገሞራ ኀጢ​አት ተቃ​ወ​መ​ቻ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ተገ​ልጣ ታወ​ቀች።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወይን ቦታ እርሱ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ነው፤ ተወ​ዳጁ አዲስ ተክ​ልም የይ​ሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍር​ድን ያደ​ር​ጋል ብየ እጠ​ብቅ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ዐመ​ፅን አደ​ረገ፤ ጽድ​ቅ​ንም አይ​ደ​ለም፥ ጩኸ​ትን እንጂ።


አቤቱ! ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዙ ነውና፥ በአ​ን​ተም ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና ኀጢ​አ​ታ​ችን ተቃ​ው​ሞ​ናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድ​ርግ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ነቢ​ያት ላይ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥን ነገር አይ​ቻ​ለሁ፤ ያመ​ነ​ዝ​ራሉ፤ በሐ​ሰ​ትም ይሄ​ዳሉ፤ ማንም ከክ​ፋቱ እን​ዳ​ይ​መ​ለስ የክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችን እጅ ያበ​ረ​ታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም እንደ ገሞራ ሆኑ​ብኝ።


ታላ​ቂ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በስተ ግራሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰማ​ርያ ናት፤ ታና​ሽ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰዶም ናት።


መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”


“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥ​ቶ​አ​ልና ለእ​ነ​ርሱ ስበክ።”


እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፤ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ጸባዖት ጆሮ ገብቶአል።