ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።
ገላትያ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፤ “ብትገዘሩም በክርስቶስ ዘንድ ምንም አይጠቅማችሁም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፥ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ! እኔ ጳውሎስ የምላችሁ ይህ ነው፤ “መገረዝ ያስፈልገናል” ብላችሁ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፦ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። |
ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።
ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገዘሩ ዘንድና የኦሪትንም ሕግ ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው በነገር እንደ አወኩአችሁና ልባችሁን እንደ አናወጡት ሰምተናል።
ነገር ግን ካመኑት ከፈሪሳውያን ወገን አንዳንዶች ተነሥተው፥ “ትገዝሩአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዝዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ጳውሎስ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ብርቅ ግን የምደፍራችሁ በክርስቶስ የዋህነትና ቸርነት እማልዳችኋለሁ፥ በፍቅራችሁ እታመናለሁና።
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ግዝረትን ገና የምሰብክ ከሆነ፥ እንግዲህ ለምን ያሳድዱኛል? እንግዲህ የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት እንዲያው ቀርቶአል።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በፍቅር የምትሠራ እምነት እንጂ መገዘር አይጠቅምምና፤ አለመገዘርም ግዳጅ አይፈጽምምና።
ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛም የምሥራች ተሰብኮልናል፤ ነገር ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።