በአዕማዱም ራስ ላይ የነበሩትን ጕልላቶች ይሸፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መርበብ ሥራ አደረገ፤ አንዱም መርበብ ለአንዱ ጕልላት፥ ሁለተኛውም መርበብ ለሁለተኛው ጕልላት ነበረ።
ዘፀአት 28:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ቋዶችንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጐነጐነ ገመድ አድርገህ ሥራ፤ የተጐነጐኑትንም ቋዶች በፈርጦቹ ላይ አንጠልጥል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገመድ ያሉ ሁለት በንጹሕ ወርቅ የተጐነጐኑ ድሪዎችን አብጅተህ ከፈርጡ ጋራ አያይዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ተጎነጎነ ገመድ አድርገህ ሁለት ድሪዎች ከንጹሕ ወርቅ ሥራ፤ የተጎነጎኑትንም ድሪዎች ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ገመድ ተጐንጒነው ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ሁለት ድሪዎችንም አበጅተህ ከሁለቱ ፈርጦች ጋር እንዲያያዙ አድርግ። |
በአዕማዱም ራስ ላይ የነበሩትን ጕልላቶች ይሸፍኑ ዘንድ ሁለት እንደ መርበብ ሥራ አደረገ፤ አንዱም መርበብ ለአንዱ ጕልላት፥ ሁለተኛውም መርበብ ለሁለተኛው ጕልላት ነበረ።
የአንዱም ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የናስም ጕልላት ነበረበት፤ የጕልላቱም ርዝመት ሦስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው የናስ መርበብና ሮማኖች ነበሩ፤ እንዲሁም ደግሞ በሁለተኛው ዓምድ ላይ መርበብ ነበረበት።
በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
“ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን ልብሰ እንግድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መትከፍም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍታም ሥራው።