La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 25:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በስርየት መክደኛው ዳርና ዳር ላይ የሚሆኑ ከወርቅ የተቀረጹ ሁለት ኪሩቤል ሥራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከተቀጠቀጠም ወርቅ ክንፎች ያሉአቸው የሁለት ኪሩቤል ምስል ሥራ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 25:18
15 Referencias Cruzadas  

አዳ​ም​ንም አስ​ወ​ጣው፤ ደስታ በሚ​ገ​ኝ​ባት በገ​ነት አን​ጻ​ርም አኖ​ረው፤ ወደ ሕይ​ወት ዛፍ የሚ​ወ​ስ​ደ​ው​ንም መን​ገድ ለመ​ጠ​በቅ የም​ት​ገ​ለ​ባ​በጥ የነ​በ​ል​ባል ሰይ​ፍን በእ​ጃ​ቸው የያዙ ኪሩ​ቤ​ልን አዘ​ዛ​ቸው።


ለዕ​ጣ​ኑም መሠ​ዊያ ጥሩ​ውን ወርቅ በሚ​ዛን፥ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት የሸ​ፈ​ኑ​ትን የኪ​ሩ​ቤ​ልን የወ​ርቅ ሰረ​ገላ ምሳሌ አሳ​የው።


በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ውስጥ ከእ​ን​ጨት ሥራ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው።


ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሥራ።


ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ጋር አን​ዱን ኪሩብ በአ​ንድ ወገን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ በሌ​ላው ወገን አድ​ር​ገህ በአ​ንድ ላይ ትሠ​ራ​ዋ​ለህ፤ ሁለ​ቱ​ንም ኪሩ​ቤል እን​ዲሁ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


ጕብ​ጕ​ቦ​ቹና ቅር​ን​ጫ​ፎቹ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ይሁኑ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ከጥሩ ወርቅ ይደ​ረግ።


በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን ሰው፥ “በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች መካ​ከል በኪ​ሩብ በታች ግባ፤ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል ከአ​ለው እሳት ፍም እጆ​ች​ህን ሙላ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ላይ በት​ነው” ብሎ ተና​ገ​ረው። እኔም እያ​የሁ ገባ።


ይህ በኮ​ቦር ወንዝ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በታች ያየ​ሁት እን​ስሳ ነው፤ ኪሩ​ቤ​ልም እንደ ነበሩ ዐወ​ቅሁ።


ሰው​የ​ውም ሲገባ ኪሩ​ቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፤ ደመ​ና​ውም ውስ​ጠ​ኛ​ውን አደ​ባ​ባይ ሞላ።


በላ​ይ​ዋም ማስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ውን የሚ​ጋ​ርዱ የክ​ብር ኪሩ​ቤል ነበሩ፤ ነገር ግን በየ​መ​ልኩ እና​ገ​ረው ዘንድ ዛሬ ጊዜው አይ​ደ​ለም።


ሕዝ​ቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።