ወደ እርሱም ቀረበ፤ ሳመውም፤ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፤ ባረከውም፤ እንዲህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
ዘዳግም 33:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፦ ምድሩ ከእግዚአብሔር በረከት፥ ከሰማይ ዝናምና ጠል፥ ከታችም ከጥልቁ ምንጭ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ “እግዚአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ድንቅ የሆነውን ጠል ከላይ ከሰማይ በማውረድ፣ ከታች የተንጣለለውን ጥልቅ ውሃ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ “ምድሩ ከጌታ ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ ከሰማያት በሚዘንበው የላቀ ስጦታ፥ ከታችም ከጥልቀት ከሚገኘው ውሃ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ዮሴፍም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ከላይ በሰማይ በሚዘንብ ዝናብ፥ ከታችም ከጥልቀት በሚገኘው ውሃ፥ ምድራቸውን ይባርክ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ 2 ምድሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረከ ይሁን፤ 2 በሰማያት ገናንነት በጠል፥ 2 በታችኛውም ቀላይ፥ |
ወደ እርሱም ቀረበ፤ ሳመውም፤ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፤ ባረከውም፤ እንዲህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
ዮሴፍም ለአባቱ ፥ “እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው። ያዕቆብም፥ “እባርካቸው ዘንድ ወደ እኔ አቅርብልኝ” አለው።
የያዕቆብም ቅሬታ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውንም እንደማይጠብቅ፥ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ይሆናል።
ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።
የምናሴ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች- እንደ እየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥
ትምህርቴንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድርገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይውረድ፤ በእርሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣርም ላይ እንደ ጤዛ።
እስራኤልም ተማምኖ፥ በያዕቆብ ምድር ብቻውን፥ በስንዴና በወይን ምድር ይኖራል፤ ሰማይ ከደመናና ከጠል ጋር ለአንተ ነው።