አንተ ግን በውጭ ቁም፤ ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ወደ ውጭ ያውጣልህ።
አንተ ከውጭ ሆነህ ጠብቅ፤ ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ከቤት ያምጣልህ።
አንተ ውጪ ቈይ፤ እርሱ ራሱ መያዣውን ያምጣልህ።
አንተ በውጭ ቁም ያበደርኸውም ሰው መያዣውን ያውጣልህ።
ብዙዎችን የተራቈቱትንም ያለ ልብስ ያሳድሩአቸዋል። መጐናጸፊያቸውንም ይገፍፏቸዋል።
“ለባልንጀራህ ባበደርኸው ጊዜ መያዣውን ልትወስድ ወደ ቤቱ አትግባ።
ያም ሰው ድሃ ቢሆን መያዣውን በአንተ ዘንድ አታሳድር።