ዘዳግም 23:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባትሳል ግን ኀጢአት የለብህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳትሳል ብትቀር ግን በደለኛ አትሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ለእግዚአብሔር ስእለት አለማድረግ ራሱ ኃጢአት አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም። |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰውነቱ ዋጋውን ይስጥ።
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኀጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘግይ።
በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።
የማኅበሩም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልገደሉአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጕረመረሙ።