ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆም መጡ፤ አዩኣትም፤ ከዚያም ከወይኑ አንድ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፤ በመሎጊያም ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።
ዘዳግም 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ‘ተነሡና ተጓዙ፤ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ የዛሬድንም ፈፋ ተሻገርን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እግዚአብሔር “አሁኑኑ ተነሡና የዘሬድን ደረቅ ወንዝ ተሻገሩ” አለን፤ እኛም ወንዙን ተሻገርን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁንም፥ ‘ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ አለን። የዘሬድንም ፈፋ ተሻገርን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በነገረን መሠረት የዘሬድን ወንዝ ተሻገርን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ አለ። |
ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆም መጡ፤ አዩኣትም፤ ከዚያም ከወይኑ አንድ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፤ በመሎጊያም ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።
ከዚያም ተጕዘው ከአሞራውያን ዳርቻ በሚወጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።
ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፤ የዔሳው ልጆች ግን መቱአቸው፤ ከፊታቸውም አጠፉአቸው፤ እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ በስፍራቸው ተቀመጡ።
የዛሬድንም ፈፋ እስከ ተሻገርንበት ድረስ፥ እግዚአብሔር እንደ ማለባቸው ተዋጊዎች የሆኑ የዚያች ትውልድ ሰዎች ከሰፈሩ መካከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃዴስ በርኔ የተጓዝንበት ዘመን ሠላሳ ስምንት ዓመት ሆነ።