Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 2:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በነገረን መሠረት የዘሬድን ወንዝ ተሻገርን፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም እግዚአብሔር “አሁኑኑ ተነሡና የዘሬድን ደረቅ ወንዝ ተሻገሩ” አለን፤ እኛም ወንዙን ተሻገርን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “አሁንም፥ ‘ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ አለን። የዘሬድንም ፈፋ ተሻገርን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አሁ​ንም ‘ተነ​ሡና ተጓዙ፤ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገሩ፤’ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገ​ርን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 2:13
5 Referencias Cruzadas  

ከዚያም አልፈው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ።


አልፈውም ወደ ኤሾኮል ሸለቆ ደረሱ፤ ከዚያም የወይን ዘለላ ያለበትን ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ያንንም የወይን ዘለላ አንድ ሰው ብቻውን ሊሸከመው የማይችል ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሁለት ሰዎች በመሎጊያ በትከሻቸው ላይ ተሸከሙት፤ ከዚህም ጋር የሮማንና የበለስ ፍሬ ይዘው መጡ።


ሖራውያንም በኤዶም ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን የዔሳው ዘሮች ሖራውያንን ነቃቅለው በማባረር በእነርሱ ቦታ ሰፍረውበት ነበር፤ ይኸውም እስራኤላውያን ዘግየት ብለው እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ እንዳደረጉት ዐይነት መሆኑ ነው።]


ይህም የሆነው ቃዴስ በርኔን ትተን ከሄድን ከሠላሳ ስምንት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው፤ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ አስቀድሞ በመሐላ በተናገረው መሠረት ለጦርነት የደረሱ የዚያ ትውልድ ወንዶች ሁሉ አልቀው ነበር።


ከዚያም ተጒዘው እስከ አሞራውያን ግዛት በሚዘልቀው ምድረ በዳ ከአርኖን ወንዝ ማዶ በሚገኘው ቦታ ሰፈሩ፤ የአርኖን ወንዝ በሞአባውያንና በዐሞራውያን ግዛት ወሰን ላይ የሚገኝ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios