የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መዋረዴንና የእጆችን ድካም አየ፤ ትናንትም ገሠጸህ።”
ዘዳግም 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአንተም ዘንድ አርነት አውጥተህ በለቀቅኸው ጊዜ ባዶውን አትልቀቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምታሰናብተውም ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነጻ በምታወጣው ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነጻ በምታወጣው ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንተም ዘንድ አርነት ባወጣኸው ጊዜ ባዶውን አትስደደው፤ |
የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሀት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መዋረዴንና የእጆችን ድካም አየ፤ ትናንትም ገሠጸህ።”
ቤቱን በዐመፅ፥ አዳራሹንም ያለ እውነት ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው ወዮለት!
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፣ በመተተኞችና በአመንዝሮች፥ በሐሰትም በሚምሉ፥ የምንደኛውን ደመመዝ በሚከለክሉ፥ መበለቲቱንና ድሀ አደጉን በሚያስጨንቁ፥ የመጻተኛውንም ፍርድ በሚያጣምሙ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“አንተም ወንድምህን ዕብራዊዉን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግሉህ፤ በሰባተኛውም ዓመት ከአንተ ዘንድ አርነት አውጥተህ ልቀቀው።
ነገር ግን ከበጎችህ፥ ከእህልህም፥ ከወይንህም መጭመቂያ ስንቅ ትሰንቅለታለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ።
ጌቶች ሆይ፥ ለአገልጋዮቻችሁ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ እውነትንም ፍረዱ፤ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና።