ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮረብታው ላይ ይሠዋና ያጥን ነበር።
ዘዳግም 11:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፣ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትወድዱና በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል በታማኝነት ብትጠብቁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም ዛሬ እኔ የማዛችሁን ሕግ ሁሉ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁንም ውደዱ፤ በፍጹም ልባችሁም አገልግሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ |
ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮረብታው ላይ ይሠዋና ያጥን ነበር።
እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ፥ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩባት፥
እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች እባርካቸዋለሁ፤ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፤ የበረከትም ዝናብ ይሆናል።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እርሱንም ትከተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥
“በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበዙም ዘንድ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ዮርዳኖስን የምትሻገሩላትን ምድር እንድትወርሷት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤
“እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ፥ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።
ነገር ግን ከዚያ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትሻላችሁ፤ በመከራህም ጊዜ በልብህም ሁሉ፥ በነፍስህም ሁሉየፈለግኸው እንደ ሆነ ታገኘዋለህ።
“እንዲህም ይሆናል፤ ይህችን ፍርድ ሰምታችሁ ብትጠብቋት፥ ብታደርጓትም፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ የማለውን ቃል ኪዳንና ምሕረት ለእናንተ ይጠብቅላችኋል፤