La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ በግ​ብፅ ሀገር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስለ​ዚህ ስደ​ተ​ኛ​ውን ውደዱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና መጻተኛን ውደዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ፥ እናንተ በግብጽ አገር ስደተኞች ነበራችሁና፥ ስደተኛውን ውደዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም እናንተም ለእነዚህ ስደተኞች ፍቅራችሁን ልታሳዩአቸው ይገባል፤ እናንተም ራሳችሁ በግብጽ ምድር መጻተኞች የሆናችሁበት ጊዜ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ በግብፅ አገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 10:19
12 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ በግ​ብፅ ምድር ስደ​ተ​ኞች ነበ​ራ​ች​ሁና ስደ​ተ​ኛ​ውን አት​በ​ድ​ሉት፤ ግፍም አታ​ድ​ር​ጉ​በት።


ለእ​ና​ን​ተና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ለሚ​ቀ​መጡ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ልጆ​ችን ለሚ​ወ​ልዱ መጻ​ተ​ኞች ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ በዕጣ ትካ​ፈ​ሉ​አ​ታ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል እንደ አሉ የሀ​ገር ልጆች ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች መካ​ከል ከእ​ና​ንተ ጋር ርስ​ትን ይወ​ር​ሳሉ።


መጻ​ተ​ኛ​ውም በማ​ና​ቸ​ውም ነገድ መካ​ከል ቢቀ​መጥ በዚያ ርስ​ትን ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ችሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወገኑ ሌላ ከሆነ ከዚህ ሰው በቀር ለእ​ነ​ዚያ ተመ​ልሶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገን ተሳ​ና​ቸ​ውን?”


አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።


እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።


“ኤዶ​ማ​ዊዉ ወን​ድ​ምህ ነውና አት​ጸ​የ​ፈው፤ ግብ​ፃ​ዊ​ዉ​ንም በሀ​ገሩ ስደ​ተኛ ነበ​ር​ህና አት​ጸ​የ​ፈው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በሦ​ስ​ተ​ኛው ትው​ልድ የሚ​ወ​ለዱ ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይግቡ።