La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን በፊ​ታ​ችሁ እንደ ሰጣ​ችሁ እዩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ላ​ችሁ ውጡ፤ ውረ​ሷት፤ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ሰጥቷችኋል፤ አሁንም የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በነገራችሁ መሠረት ውጡ፤ ውረሷትም፤ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ ጌታ አምላካችሁ ምድሪቱን በፊትህ አኑሮአል፥ የአባቶችህ አምላክ ጌታ እንዳለህ፥ ውጣ፥ ውረሳት፥ አትፍራ፥ አትደንግጥም።’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ተመልከቱ፤ አገሪቱ ይህችውላችሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ገብታችሁ ውረሱአት፤ በመፍራትም ተስፋ አትቊረጡ።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ምድሪቱን በፊትህ አድርጎአል፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እንዳለህ፥ ውጣ፥ ውረሳት፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም አልኋችሁ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 1:21
20 Referencias Cruzadas  

ለራ​ባ​ቸ​ውም ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ከዓ​ለቱ ውኃን አወ​ጣ​ህ​ላ​ቸው፤ ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጅ​ህን የዘ​ረ​ጋ​ህ​ባ​ትን ምድር ገብ​ተው ይወ​ር​ሷት ዘንድ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።


አሕ​ዛብ ሁላ​ችሁ፥ እጆ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ብ​ጭቡ፥ በደ​ስታ ቃልም ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማ​ስ​ተ​ዋል ዘምሩ፤


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ካሌ​ብም ሕዝ​ቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰ​ኘና፥ “አይ​ደ​ለም! ማሸ​ነ​ፍን እን​ች​ላ​ለ​ንና እን​ውጣ፤ እን​ው​ረ​ሳት” አለ።


“አንተ ታናሽ መንጋ፥ አት​ፍራ፤ አባ​ታ​ችሁ መን​ግ​ሥ​ቱን ሊሰ​ጣ​ችሁ ወዶ​አ​ልና።


እኔም አል​ኋ​ችሁ፦ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ሰጣ​ችሁ እስከ አሞ​ሬ​ዎን ተራራ ኑ፤


“ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።


እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ዛሬ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ለመ​ው​ጋት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ችሁ አይ​ታ​ወክ፤ አት​ፍሩ፤ አት​ሸ​በሩ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም ፈቀቅ አት​በሉ፤


ጽና፤ በርታ፤ አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ፤ አት​ድ​ከም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከአ​ንተ ጋር ይሄ​ዳል፤ አይ​ጥ​ል​ህም፤ አይ​ተ​ው​ህ​ምም።


ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ያደ​ረ​ገ​ውን ፈጽ​መህ አስብ፤


ከፊ​ታ​ቸው አት​ደ​ን​ግጥ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ እር​ሱም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅና ጽኑዕ ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ውጡ፤ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁ​ንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ካ​ችሁ ጊዜ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዐመ​ፃ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም አላ​መ​ና​ች​ሁም፤ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


አሁ​ንም አም​ነን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?” እን​በል።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”