አሞጽ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ መሠረቶችዋንም ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሽጎቿን እንዲበላ፣ በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰድዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የእርሷንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በጋዛ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጋዛ ቅጥር ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፥ አዳራሾችዋንም ትበላለች። |
ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትን ቅጥር፥ የኢያቢስንም ቅጥር፥ የአዛጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም ሀገር ከተሞችን ሠራ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በኤዶምያስ ይዘጉባቸው ዘንድ የሰሎሞንን ምርኮ ማርከዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
የአዛጦን ነዋሪዎችን አጠፋለሁ፤ የአስቀሎናም ሕዝብ ይጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፤ ከፍልስጥኤማውያን የቀሩትም ይጠፋሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።