ስለዚህም ወዲያውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመምጣትህም መልካም አደረግህ፤ አሁንም እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ ልንሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”
ሐዋርያት ሥራ 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘አቤቱ፥ ጌታዬ ምን ላድርግ?’ አልሁ፤ ጌታም፦ ‘ተነሥና ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ልታደርገው የሚገባህንም ሁሉ በዚያ ይነግሩሃል’ አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ምን ላድርግ?’ አልሁት። “ጌታም፣ ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህ ሁሉ ይነገርሃል’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ጌታ ሆይ! ምን ላድርግ?’ አልሁት። ጌታም ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድና ታደርገው ዘንድ ስለ ታዘዘው ሁሉን በዚያ ይነግሩሃል፤’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ‘ጌታ ሆይ! ምን ላድርግ?’ አልኩ። ጌታም ‘ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ልታደርገው የሚገባህ ነገር ሁሉ እዚያ ይነገርሃል’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ ሆይ፥ ምን ላድርግ? አልሁት። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድና ታደርገው ዘንድ ስለ ታዘዘው ሁሉን በዚያ ይነግሩሃል አለኝ። |
ስለዚህም ወዲያውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመምጣትህም መልካም አደረግህ፤ አሁንም እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ ልንሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላችን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን።”
ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው።
እርሱም እየፈራና እየተንቀጠቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እንዳደርግ ትሻለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ይነግሩሃል” አለው።