La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 6:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ በእ​ል​ልታ ቀንደ መለ​ከት እየ​ነፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አመ​ጡ​አት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህ ባለ ሁኔታም ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት ሆይ እያሉና ቀንደ መለከቱን እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህ ባለ ሁኔታም ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት እየጨፈሩና ቀንደ መለከቱን እየነፉ የጌታን ታቦት አመጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህም ዐይነት ዳዊትና መላው እስራኤል በደስታ እልል እያሉና የእምቢልታ ድምፅ እያሰሙ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ይዘው ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ ሆ እያሉ ቀንደ መለከትም እየነፋ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 6:15
16 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በገና ይደ​ረ​ድር ነበር፤ ዳዊ​ትም ለዐ​ይን የሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ የሐር ቀሚስ ለብሶ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሲዘ​ል​ልና ሲዘ​ምር አየ​ችው፥ በል​ብ​ዋም ናቀ​ችው።


ዳዊ​ትም በዜማ ዕቃ፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም እን​ዲ​ያ​ዜሙ፥ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በደ​ስታ ከፍ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ መዘ​ም​ራ​ኑን “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ሹሙ” ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ተና​ገረ።


ዳዊ​ትም፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት በደ​ስታ ያመጡ ዘንድ ሄዱ።


እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


ጻድ​ቃን በክ​ብሩ ይመ​ካሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።


በመ​ለ​ከት ድምፅ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ አመ​ስ​ግ​ኑት፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፤ በአ​ም​ላ​ካ​ችን ከተማ በመ​ቅ​ደሱ ተራራ ምስ​ጋ​ናው ብዙ ነው።


ሕዝቡ በሚ​ገ​ቡ​በት ጊዜ አለ​ቃው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይግባ፤ በሚ​ወ​ጡ​በ​ትም ጊዜ ይውጣ።


እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።