2 ሳሙኤል 18:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ሁሉ በእስራኤል ላይ ወደ በረሓ ወጡ፤ በኤፍሬምም በረሓ ተዋጓቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰራዊቱ እስራኤልን ለመውጋት ተሰልፎ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ጦርነቱም በኤፍሬም ደን ውስጥ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠራዊቱ እስራኤልን ለመውጋት ተሰልፎ ወደ ሜዳ ወጣ፤ ጦርነቱም በኤፍሬም ደን ውስጥ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊት ሠራዊት ወደ ገጠር ወጥተው እስራኤላውያንን በኤፍሬም ደን ውስጥ ተዋጉአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም በእስራኤል ላይ ወደ ሜዳ ወጣ፥ ሰልፉም በኤፍሬም ዱር ውስጥ ሆነ። |
ኢያሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ተራራማው የኤፍሬም ሀገርም ከጠበባችሁ ወደ ዱር ወጥታችሁ መንጥራችሁ አቅኑአት” አላቸው።
ነገር ግን ተራራማው ሀገር ለእናንተ ይሆናል፤ ዱር እንኳ ቢሆንም ትመነጥሩታላችሁ፤ ለእናንተም ይሆናል፤ ለከነዓናውያንም የተመረጡ ፈረሶችና የብረት ሰረገሎች ቢሆኑላቸው፥ የበረቱ ቢሆኑም እናንተ እስክታጠፉአቸው ድረስ ትበረቱባቸዋላችሁ” አላቸው።