La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 8:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ አካ​ዝ​ያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች። እርሷም የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በነገሠም ጊዜ የሀያ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ብቻ ገዛ፤ እናቱ ዐታልያ ተብላ የምትጠራው የአክዓብ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በነገሠም ጊዜ የኻያ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ብቻ ገዛ፤ እናቱ ዐታልያ ተብላ የምትጠራው የአክዓብ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መንገሥ በጀመረ ጊዜ አካዝያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም ጎቶልያ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ ልጅ ነበረች።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 8:26
8 Referencias Cruzadas  

ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ። ለጆ​ሮ​ዎ​ች​ዋም ጉት​ቻ​ዎ​ችን ለእ​ጆ​ች​ዋም አም​ባ​ሮ​ችን አድ​ርጌ አስ​ጌ​ጥ​ኋት። ደስ ባሰ​ኘ​ች​ኝም ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገ​ድሁ፤ የጌ​ታ​ዬን የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ለልጁ እወ​ስድ ዘንድ በቀና መን​ገድ የመ​ራ​ኝን የጌ​ታ​ዬን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ንሁ።


ዘን​በ​ሪ​ንም የተ​ከ​ተሉ ሕዝብ የጎ​ናት ልጅ ታምኒን የተ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሕዝብ ድል አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ታም​ኒም ሞተ፤ ወን​ድ​ሙም ኢዮ​ራም በዚ​ያው ዘመን ሞተ፤ ከታ​ምኒ በኋላ ዘን​በሪ ነገሠ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአሳ በሠ​ላሳ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ዘን​በሪ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት ነገሠ። በቴ​ር​ሳም ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


አካ​ዝ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።