2 ቆሮንቶስ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያን መትጋት የሰጠ እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን በጎ ሐሳብ በቲቶ ልብ ውስጥ ያኖረ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ለእናንተ የማስበውን ያኽል ቲቶም ለእናንተ ከልቡ እንዲያስብ ያደረገ አምላክ ይመስገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በቲቶ ልብ ስለ እናንተ ያንን ትጋት የሰጠ አምላክ ይመስገን፤ |
ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም።
ከእነርሱም እንዳልመለስ፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
ይህን የጻፍሁላችሁ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋችሁ ይታወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደለና ስለ ተበደለ ሰው አይደለም።
በመምጣቱ ብቻ አይደለም፤ በአጽናናችሁት ማጽናናትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እንደምታስቡና እንደምትቀኑ ፍቅራችሁን ነግሮናል፤ ይህንም ሰምቼ ደስታዬ በእናንተ በዛ።
ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ጓደኛዬ ነው፥ ወንድሞቻችንም ቢሆኑ፥ ለእግዚአብሔር ክብር የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት ናቸው።
በቃልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ፤ ስለ እርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑት።
እግዚአብሔር አሳቡን እንዲያደርጉ አንድንም አሳብ እንዲያደርጉ የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ መንግሥታቸውን ለአውሬው እንዲሰጡ በልባቸው አገብቶአልና።