“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
2 ቆሮንቶስ 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተጠራጣሪዎች አትሁኑ፤ ወደማያምኑ ሰዎች አንድነትም አትሂዱ፤ ጽድቅን ከኀጢአት ጋር አንድ የሚያደርጋት ማን ነው? ብርሃንንስ ከጨለማ ጋር የሚቀላቅል ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማያምኑ ሰዎች ጋራ አግባብ ባልሆነ መንገድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋራ ምን ግንኙነት አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋራ ምን ኅብረት አለው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማያምኑ ጋር አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ምን ድርሻ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማይመች ሁኔታ ከማያምኑ ሰዎች ጋር አትጣመሩ፤ ጽድቅና ኃጢአት እንዴት ሊተባበሩ ይችላሉ? ብርሃንና ጨለማ እንዴት አብረው ሊኖሩ ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? |
“እጅህን በእጄ ላይ አድርግ፤ እኔም አብሬ ከምኖራቸው ከከነዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት እንዳትወስድለት በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፤
ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በዓልም አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።
“ሥርዐቴን ጠብቁ፤ በበሬህ በባዕድ ቀንበር አትረስ፤ በወይን ቦታህ የተለያየ ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ ኀፍረት ነውና አትልበስ።
እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።
እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።
የእግዚአብሔርን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ አንድ አድርጋችሁ መጠጣት አትችሉም፤ የእግዚአብሔርን ማዕድና የአጋንንትንም ማዕድ በአንድነት ልትበሉ አትችሉም።
ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሠረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወደደችውን ታግባ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ይሁን።
እንደ እግዚአብሔር ልጆች ንጹሓንና የዋሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማያምኑና በጠማሞች ልጆች መካከል ነውር ሳይኖርባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ፤
አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።