ሞት ሰዎችን ዋጠ፤ በረታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር በአፉ ተናግሮአልና።
2 ቆሮንቶስ 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ቤት ውስጥ ሳለንም ከከባድነቱ የተነሣ እጅግ እናዝናለን፤ ነገር ግን ሟች በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንወድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ድንኳን እስካለን ድረስ ከብዶን እንቃትታለን፤ ምክንያቱም ሟች የሆነው በሕይወት እንዲዋጥ ሰማያዊውን መኖሪያችንን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ አንፈልግም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነትም የሚሞተው በሕይወት እንዲዋጥ፥ ጨምረን ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለሆነ፥ በዚህ ድንኳን ሳለን ከብዶን እንቃትታለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ እንደ ምድራዊ ድንኳን በሆነው ሥጋችን ውስጥ ስንኖር ከብደን እንቃትታለን፤ የምንቃትተውም ሞት በሕይወት እንዲለወጥ ሰማያዊውን አካል በበለጠ እንድንለብስ ነው እንጂ ከዚህ ከምድራዊ ሥጋችን ለመለየት በመፈለግ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን። |
ሞት ሰዎችን ዋጠ፤ በረታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር በአፉ ተናግሮአልና።
የቀረውንም ኑሬዬን አጣሁ። ከእኔም ወጣች፥ ተለየችም። ድንኳኑን ተክሎ እንደሚያድርና እንደሚሄድ፥ ሊቈረጥ እንደ ተቃረበ ሸማም እንዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።
ነገር ግን የሚተክዝ ዓለም ብቻ አይደለም፤ የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ የተቀበልነው እናም ደግሞ እናዝናለን እንጂ፤ የነፍሳችንን ድኅነት እናገኝ ዘንድ የልጅነትን ክብር ተስፋ እናደርጋለንና፤ በእምነትም ድነናልና።