2 ቆሮንቶስ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሜን ቲቶን ስላላገኘሁት ለሰውነቴ ዕረፍት አላገኘሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ ተለይች ወደ መቄዶንያ ሄድሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ወንድሜን ቲቶን እዚያ ስላላገኘሁት መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ ተሰናብቻቸው ወደ መቄዶንያ ሄድሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን መንፈሴ ማረፍ አልቻለም፤ ምክንያቱም እዚያ ወንድሜን ቲቶን አላገኘሁትም። ስለዚህ ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወንድሜን ቲቶን ባለማግኘቴ መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ እዚያ ያሉትን ክርስቲያኖች ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ሄድኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ። |
እነሆ ቲቶን ማለድሁት፤ ከእርሱም ጋር ሌላውን ወንድማችንን ላክሁት፤ በውኑ ቲቶ የበደላችሁ በደል አለን? በእርሱ በአደረው መንፈስ የምንመላለስ፥ እርሱም የሄደበትን ፍለጋ የምንከተል አይደለንምን?
ስለዚህም ተጽናንተናል፤ በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፤ በሁላችሁ ዘንድ ሰውነቱን አሳርፋችኋታልና።
ስለ እናንተ ለእርሱ በተመካሁበት ሁሉ አላሳፈራችሁኝምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትምክህታችን እውነት ሆነ።
ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ጓደኛዬ ነው፥ ወንድሞቻችንም ቢሆኑ፥ ለእግዚአብሔር ክብር የአብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያት ናቸው።
በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።