La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 31:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጀግኖቻቸው ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሙሉ ተጓዙ፤ የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከቤትሳን ግንብ ላይ አውርደው ወደ ኢያቢስ አምጥተው አቃጠሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጀግኖቻቸው ሁሉ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ። የሳኦልንና የልጆቹንም ሬሳ ከግንቡ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ አምጥተው አቃጠሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጀግኖቻቸው በድንገት ተነሥተው በመገሥገሥ በሌሊት ወደ ቤትሻን ሄዱ፤ የሳኦልንና የልጆቹን አስከሬን ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ላይ አውርደው ወደ ያቤሽ በማምጣት አቃጠሉአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥ የሳኦልንም ሬሳ የልጆቹንም ሬሳ ከቤትሳን ቅጥር ላይ አወረዱ፥ ወደ ኢያቢስም መጡ፥ በዚያም አቃጠሉት።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 31:12
6 Referencias Cruzadas  

ጽኑ​ዓን ሰዎች ሁሉ ከገ​ለ​ዐድ ተነ​ሥ​ተው የሳ​ኦ​ልን ሬሳ የል​ጆ​ቹ​ንም ሬሳ​ዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ካለው ከት​ልቁ ዛፍ በታች አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።


ለእ​ር​ሱም ለራሱ በሠ​ራው መቃ​ብር በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ በቀ​ማሚ ብል​ሃት የተ​ሰ​ናዳ ልዩ ልዩ መል​ካም ሽቱ በተ​ሞላ አልጋ ላይም አኖ​ሩት፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የቀ​ብር ሥር​ዐት አደ​ረ​ጉ​ለት።


ነገር ግን በሰ​ላም ትሞ​ታ​ለህ፥ ከአ​ንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገ​ሥ​ታት አባ​ቶ​ችህ እሳት ይቃ​ጠ​ል​ላ​ቸው እንደ ነበር እን​ዲሁ ያቃ​ጥ​ሉ​ል​ሃ​ልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ እኔ ቃልን ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተ​ሰ​ቦ​ቻ​ቸው በወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባ​ቂ​ውን በአ​ንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአ​ለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እን​ዳ​ት​ጠራ ዝም በል ይለ​ዋል።


የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም በአ​ስ​ታ​ሮት መቅ​ደስ ውስጥ አኖ​ሩት። ሬሳ​ው​ንም በቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉት።