1 ሳሙኤል 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “አትፍሪ ፤ ንገሪኝ፤ ማንን አየሽ?” አላት። ሴቲቱም፥ “አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትዮዋም፣ “መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትዮዋም፥ “አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “አይዞሽ አትፍሪ! ይልቅስ የምታዪው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እኔ አንድ መለኮታዊ ግርማ ያለው ከመቃብር ሲወጣ እያየሁ ነኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ አትፍሪ፥ ያየሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፦ አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ አለችው። |
ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየች ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲቱም ሳኦልን፥ “አንተ ሳኦል ስትሆን ለምን አታለልኸኝ?” ብላ ተናገረችው።
እርሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እርስዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማግሌ ሰው ከምድር ወጣ፤ መጐናጸፊያም ተጐናጽፎአል” አለች። ሳኦልም ሳሙኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊቱም ወደ ምድር ጐንበስ ብሎ ሰገደለት።