የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ፥ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።
1 ነገሥት 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከንፈሩም በታች ለአንድ ክንድ ዐሥር፥ ለአንድ ክንድም ዐሥር ጕብጕቦች አዞረበት፤ ከንፈሮቹም እንደ ጽዋ ከንፈር ነበሩ። በውስጡም አበቦች በቅለውበት ነበር። ውፍረቱም ስንዝር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከገንዳው ከንፈር በታችም፣ በእያንዳንዱ ክንድ ላይ እንደ ቅል ያሉ ዐሥር ቅርጾች ዙሪያውን በሁለት ረድፍ ከብበውታል፤ እነዚህም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ተሠርተው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገንዳው አፍ ውጫዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ፥ ቅርጾች ነበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የገንዳው አፍ ውጫዊ ክፈፍ ሁሉ ከገንዳው ጋር አንድ ወጥ ሆነው በቅል አምሳል ከነሐስ የተሠሩና በሁለት ረድፍ የተደረደሩ፥ ቅርጾች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከንፈሩም በታች ለአንድ ክንድ ዐሥር ለአንድ ክንድም ዐሥር ጉብጉቦች አዞረበት፤ እርሱም በቀለጠ ጊዜ ጉብጉቦቹ በሁለት ተራ ከእርሱ ጋር አብረው ቀልጠው ነበር። |
የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ፥ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።
በበታችዋም፥ በዙሪያዋ በዐሥሩ ክንድ የበሬዎች ምስሎች ነበሩ። ኵሬዋንም ይከብቡአት ነበር። በሬዎቹም በሁለት ተራ ሁነው ከኵሬው ጋር በአንድነት ቀልጠው የተሠሩ ነበሩ።
አንተም ተዋጊዎችን ሁሉ በዙሪያው አሰልፋቸው። ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ በከተማዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ።