La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በግ​መ​ሎ​ችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ጣች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ ነገ​ረ​ችው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታላቅ አጀብ አስከትላ ሽቱ፣ እጅግ ብዙ ወርቅና የከበሩ ድንጋዮችን በግመሎች አስጭና ኢየሩሳሌም ከደረሰች በኋላ፣ ወደ ሰሎሞን ገብታ በልቧ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫኑ ሽቶ፥ የከበረ ዕንቁና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በሐሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ብዙ የክብር አጃቢዎችን በማስከተል በግመሎች የተጫነ ሽቶ፥ የከበረ ዕንቊና ብዙ ወርቅ ይዛ መጣች፤ ከሰሎሞንም ጋር በተገናኙ ጊዜ በሐሳብዋ ያለውን ጥያቄ ሁሉ አቀረበችለት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በግመሎችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቁ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፤ ወደ ሰሎሞንም በመጣች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 10:2
15 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።


ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ እጅ​ግም ብዙ ሽቶ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳባ ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አል​መ​ጣም ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም የጠ​የ​ቀ​ች​ውን ሁሉ ፈታ​ላት፤ ያል​ተ​ረ​ጐ​መ​ላ​ትና ከን​ጉሡ የተ​ሰ​ወረ ነገር አል​ነ​በ​ረም።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ነ​ርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም ሁሉ፥ ብሩ​ንና ወር​ቁ​ንም፥ ሽቱ​ው​ንና የከ​በ​ረ​ው​ንም ዘይት፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ንዕ​ማ​ንን፥ “ሂድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ደብ​ዳቤ እል​ካ​ለሁ” አለው። እር​ሱም ሄደ፤ ዐሥ​ርም መክ​ሊት ብር፥ ስድ​ስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥ​ርም መለ​ወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።


ንዕ​ማ​ንም በፈ​ረ​ሱና በሰ​ረ​ገ​ላው መጣ፤ በኤ​ል​ሳ​ዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ።


“በመ​ከራ ሳለህ ነገር አታ​ብዛ፥ የነ​ገር ብዛት ምን ይጠ​ቅ​ም​ሃል?


ተቈጡ፥ ነገር ግን አት​በ​ድሉ፤ በመ​ኝ​ታ​ችሁ ሳላ​ችሁ በል​ባ​ችሁ የም​ታ​ስ​ቡት ይታ​ወ​ቃ​ችሁ።


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤


የመ​ብ​ራ​ትም ዘይት፥ ለቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትና ለጣ​ፋጭ ዕጣን ቅመም፥


ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ።


የሳ​ባና የራ​ዕማ ነጋ​ዴ​ዎች እነ​ዚህ ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ንግ​ድ​ሽን በጥሩ ሽቱና በከ​በረ ድን​ጋይ ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም አደ​ረጉ።


እነ​ር​ሱም ይህን ሲነ​ጋ​ገ​ሩና ሲመ​ራ​መሩ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ እነ​ርሱ ቀረበ፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ሄደ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመ​ሳ​ፍ​ን​ቱና ከከ​ተ​ማው ታላ​ላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ።