አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
1 ነገሥት 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴራውም ከሶርህያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ነበረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ይረዱት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዶንያስ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋራ ተመካከረ፤ እነርሱም ድጋፋቸውን ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሴረ፤ እነርሱም አዶንያስን ደገፉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ጉዳይ ከጸሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም ዓላማውን ደገፉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴራውም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ነበረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ይረዱት ነበር። |
አቤሴሎምም መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ወደ ነበረው ጌሎናዊው አኪጦፌል ወደ ከተማው ጊሎ ላከ። ሴራውም ጽኑ ሆነ፤ ከአቤሴሎምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።
እነሆ፥ ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያ ከአንተ ጋር ናቸው። ከንጉሡ ቤትም የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ንገራቸው።
ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ፥ “ሱነማዪቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኚለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት፤ ካህኑም አብያታርና የሶርህያ ልጅ የጭፍሮች አለቃ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው” አላት።
ዳዊትም ኢያቡሳውያንን አስቀድሞ የሚመታ ሰው አለቃና መኰንን ይሆናል አለ። የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ አስቀድሞ ወጣና ወጋቸው፥ አለቃም ሆነ።