Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ስለዚህም ጉዳይ ከጸሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም ዓላማውን ደገፉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አዶንያስ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋራ ተመካከረ፤ እነርሱም ድጋፋቸውን ሰጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህ ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር አሴረ፤ እነርሱም አዶንያስን ደገፉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሴራ​ውም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከኢ​ዮ​አ​ብና ከካ​ህኑ ከአ​ብ​ያ​ታር ጋር ነበረ፤ እነ​ር​ሱም አዶ​ን​ያ​ስን ተከ​ት​ለው ይረ​ዱት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሴራውም ከጽሩያ ልጅ ከኢዮአብና ከካህኑ ከአብያታር ጋር ነበረ፤ እነርሱም አዶንያስን ተከትለው ይረዱት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:7
12 Referencias Cruzadas  

ሱሳ የቤተ መንግሥት ጸሐፊ ሲሆን፥ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤


ንጉሡም “አቢሻግን በሚስትነት እንድድርለት ብቻ ለምን ትጠይቂኛለሽ? መንግሥቴንም ጭምር እንድለቅለት ለምን አልጠየቅሽኝም? እርሱ እኮ ታላቅ ወንድሜ ነው፤ ለምን ለካህኑ አብያታርና ለኢዮአብም ልዩ አስተያየት እንዳደርግላቸው አትጠይቂላቸውም!” አላት።


እግዚአብሔርንና መሲሑን ለመቃወም የዓለም ነገሥታት ተነሣሡ፤ ሹሞቻቸውም ከእነርሱ ጋር ተባበሩ።


ዳዊትም “በመጀመሪያ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ የሚጥል ሰው የሠራዊቱ አዛዥ ይሆናል!” አለ፤ የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ በመጀመሪያ ሄዶ በኢያቡሳውያን ላይ አደጋ በመጣሉ የሠራዊቱ አዛዥ ሆነ፤


ኢዮአብ የእስራኤል ሠራዊት አዛዥ ሲሆን፥ የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ ኀላፊ ነበር፤


ካህናቱ ሳዶቅና አብያታርም በዚያው ይገኛሉ፤ በቤተ መንግሥት የምትሰማውን ነገር ሁሉ ለእነርሱ ትነግራቸዋለህ፤


አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ከንጉሥ ዳዊት አማካሪዎች አንዱ የሆነውን አኪጦፌል ተብሎ የሚጠራውን ሰው መልእክተኛ በመላክ ከጊሎ ከተማ አስጠራ፤ በንጉሡ ላይ የተጠነሰሰው ሤራ እየጠነከረ፥ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቊጥር እየጨመረ ሄደ።


የጸሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ታሪክ ጸሐፊ ነበር፤


አኪጦፌል ከሞተ በኋላም አብያታርና የበናያ ልጅ ይሆያዳዕ የንጉሡ አማካሪዎች ሆኑ፤ ኢዮአብ ደግሞ የንጉሡ ሠራዊት አዛዥ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios