La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወ​ዳ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እን​ዲህ የሆነ አለና፤ ግብሩ ሌላ የሆ​ነም አለና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን ምኞቴ ነው። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ከእግዚአብሔር የተቀበለው የራሱ የሆነ ስጦታ አለው፤ አንዱ አንድ ዐይነት ስጦታ ሲኖረው፣ ሌላው ደግሞ ሌላ ዐይነት ስጦታ አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፤ አንዱ እንደዚህ ሌላውም እንደዚያ ዓይነት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሚስት ሳያገባ ቢኖር በወደድኩ ነበር፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ እግዚአብሔር የተለየ ስጦታ ሰጥቶታል፤ አንዱ አንድ ዐይነት ስጦታ፥ ሌላውም ሌላ ዐይነት ስጦታ አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:7
9 Referencias Cruzadas  

ላባም፥ “እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን” አለ።


ጳው​ሎ​ስም፥ “በጥ​ቂ​ትም ቢሆን፥ በብ​ዙም ቢሆን አንተ ብቻ ሳት​ሆን ዛሬ የሚ​ሰ​ሙኝ ሁሉ ደግሞ ከዚህ ከእ​ስ​ራቴ በቀር እንደ እኔ እን​ዲ​ሆኑ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠን ጸጋ መጠን ልዩ ልዩ ስጦታ አለን። ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እንደ እም​ነቱ መጠን ይና​ገር።


በዚ​ህም ሁሉ ያው አንዱ መን​ፈስ ቅዱስ ሁሉን ይረ​ዳል፤ ለሁ​ሉም እንደ ወደደ ያድ​ላ​ቸ​ዋል።


መን​ፈስ ቅዱስ አንድ ሲሆን ስጦ​ታው ልዩ ልዩ ነው።


ነገር ግን ያላ​ገ​ቡ​ት​ንና አግ​ብ​ተው የፈ​ቱ​ትን እንደ እኔ ሆነው ቢኖሩ ይሻ​ላ​ቸ​ዋል እላ​ለሁ።


እኔ ግን ይህ​ንም ቢሆን አል​ፈ​ቀ​ድ​ሁ​ትም፤ ይህን የጻ​ፍ​ሁም ይህን እን​ዳ​ገኝ ብዬ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ምስ​ጋ​ናዬ ከሚ​ቀ​ር​ብኝ ሞት ይሻ​ለ​ኛል።


እንደ ሌሎች ሐዋ​ር​ያት ሁሉና፥ እንደ ጌታ​ችን ወን​ድ​ሞች እንደ ኬፋም ከሴ​ቶች እኅ​ታ​ች​ንን ይዘን ልን​ዞር አይ​ገ​ባ​ን​ምን?