La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 7:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲህ ከሆነ ግን ተለ​ያየ፤ አግ​ብታ የፈ​ታች ሴትም ያላ​ገ​ባች ድን​ግ​ልም ብት​ሆን ነፍ​ስ​ዋም ሥጋ​ዋም ይቀ​ደስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታስ​በ​ዋ​ለች፤ ያገ​ባች ግን ባል​ዋን ደስ ልታ​ሰኝ የዚ​ህን ዓለም ኑሮ ታስ​ባ​ለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህም ልቡ ተከፍሏል። ያላገባች ሴት ወይም ድንግል ስለ ጌታ ነገር ታስባለች፤ ዐላማዋም በሥጋና በመንፈስ ለጌታ መቀደስ ነው። ያገባች ሴት ግን ባሏን ደስ ለማሠኘት የዚህን ዓለም ነገር ታስባለች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ልቡም ተከፍሎአል። ያላገባች ሴትና ድንግል በሰውነት በመንፈስም እንድትቀደስ የጌታን ነገር ታስባለች፤ ያገባች ግን ባሏን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ሁኔታ ሐሳቡ በሁለት ተከፍሎአል ማለት ነው። እንዲሁም ባል ያላገባች ሴት ወይም ልጃገረድ በሥጋዋና በነፍስዋ ተቀድሳ የጌታ ለመሆን ስለምትፈልግ ሐሳቧ የሚያተኲረው ጌታን በሚመለከት ሥራ ነው። ያገባች ሴት ግን ባልዋን ለማስደሰት ስለምትፈልግ የምታስበው የዓለምን ነገር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 7:34
16 Referencias Cruzadas  

ምን​ደ​ኛስ ይሸ​ሻል፤ ስለ በጎ​ችም አያ​ዝ​ንም፤ ምን​ደኛ ነውና።


ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እንደ ተነሣ፥ ራሳ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጉ እንጂ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አት የዐ​መፅ የጦር መሣ​ሪያ አታ​ድ​ር​ጉት፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ድቅ የጦር መሣ​ሪያ አድ​ርጉ።


በዋጋ ተገ​ዝ​ታ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ጋ​ችሁ አክ​ብ​ሩት።


ያገባ ግን ሚስ​ቱን ደስ ሊያ​ሰኝ የዚ​ህን ዓለም ኑሮ ያስ​ባል።


ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ እን​ዲ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነው፤ ላጠ​ም​ዳ​ችሁ ግን አይ​ደ​ለም፤ ኑሮ​አ​ችሁ አንድ ወገን እን​ዲ​ሆ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያለ​መ​ጠ​ራ​ጠር እን​ድ​ታ​ገ​ለ​ግ​ሉት ነው እንጂ።


የቀ​ረ​ው​ንም ነገር ሳል​ቈ​ጥር ዕለት ዕለት የሚ​ከ​ብ​ድ​ብኝ የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ አሳብ ነው።


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል።


የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።


ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?


ብቻዋንም ኖራ በእውነት ባልቴት የምትሆን በእግዚአብሔር ተስፋ ታደርጋለች፤ ሌትና ቀንም በልመና በጸሎትም ጸንታ ትኖራለች፤


ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲጸኑ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤