La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አን​ተም እንደ ተና​ገ​ረው ያከ​ና​ው​ን​ልህ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“አሁንም ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሁን፤ እንድትፈጽመው በተናገረውም መሠረት፣ ተሳክቶልህ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቤት ለመሥራት ያብቃህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም፥ ልጄ ሆይ! ጌታ ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም እንደ ተናገረው ያከናውንልህ፥ የአምላክህንም የጌታን ቤት ሥራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “አሁንም ልጄ ሆይ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ ለእርሱ ቤተ መቅደስ ትሠራለት ዘንድ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ሁሉን ነገር ያከናውንልህ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም፥ ልጄ ሆይ! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ ስለ አንተም እንደ ተናገረው ያከናውንልህ፤ የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 22:11
11 Referencias Cruzadas  

ቍጥር በሌ​ለው በወ​ር​ቅና ብር፥ በና​ስና ብረት ተነ​ሥ​ተህ ሥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


ዳዊ​ትም ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን፥ “ጠን​ክር፤ ሰው ሁን፤ አይ​ዞህ፥ አድ​ር​ገ​ውም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ሆ​ነ​ውን ሥራ ሁሉ እስ​ክ​ት​ፈ​ጽም ድረስ እርሱ አይ​ተ​ው​ህም፤ አይ​ጥ​ል​ህ​ምም። እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ፥ የቤተ መዛ​ግ​ብቱ፥ የሰ​ገ​ነቱ፥ የው​ስጡ ቤተ መዛ​ግ​ብት፥ የስ​ር​የት ቤቱና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ምሳሌ።


የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ በረታ፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ እጅ​ግም አከ​በ​ረው፤ አገ​ነ​ነ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ፈጸመ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተተ​ካሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ።


አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሁሉን ሰጥ​ተ​ኸ​ና​ልና ሰላ​ምን ስጠን።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።


የሰ​ላም አም​ላክ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው።


አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።