መዝሙር 39:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ የሞኞች መሣለቂያ አታድርገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ አሁንስ ማንን እጠብቃለሁ? ተስፋዬ በአንተ ነው።። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤ ሞኞች እንዲሳለቁብኝ አታድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።” |
በእግዚአብሔር ፊት የሚያገለግሉ ካህናት፣ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አደባባይ መካከል ሆነው ያልቅሱ፤ እንዲህም ይበሉ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህን በአሕዛብ መካከል መተረቻ፣ መሣቂያና መሣለቂያም አታድርግ፤ ለምንስ በሕዝቦች መካከል፣ ‘አምላካቸው ወዴት ነው?’ ይበሉን።”
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም።