መዝሙር 113:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር፣ በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጌታ እንደ እግዚአብሔር የሚሆን ማን ነው? በላይ የሚኖር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፤ ዙፋኑም ከሁሉ በላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንተም ዮርዳኖስ ወደ ኋላህ የተመለስህ፥ ምን ሁናችሁ ነው? |
የሠራ አካላቴ እንዲህ ይልሃል፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ማን አለ? ችግረኛውን ከርሱ ከሚበረቱ፣ ችግረኛውንና ድኻውን ከቀማኞች ታድናለህ።”
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ? በቅድስናው የከበረ፣ በክብሩ የሚያስፈራ፣ ድንቆችን የሚያደርግ፣ እንደ አንተ ማን አለ?
ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።